





ወጋገን ባንክ ከከፍታ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
ጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ
ወጋገን ባንክ ከከፍታ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው ዕለት በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ተፈራረመ ፡፡
በወጋገን ባንክ በኩል ስምምነቱን የፈረሙት አቶ ኪዳኔ ገ/ሥላሴ የባንኩ የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ስራ አስፈፃሚ ሲሆኑ በከፍታ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ በኩል ደግሞ ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ሞገስ ታመነ ናቸው፡፡
በፊርማ ስነስርዓቱ ወቅት አቶ ኪዳኔ ገ/ሥላሴ ወጋገን ባንክ ከበርካታ የብድር እና ቁጠባ ተቋማት እንዲሁም ማህበራት ጋር በትብብር የመስራት የካበተ ልምዱን ተጠቅሞ ለከፍታ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡
በስምምነቱ መሰረት ወጋገን ባንክ የኮር ባንኪንግ ስርዓቱን ከከፍታ ማይክሮ ፋይናንስ ስርዓት ጋር በማስተሳሰር ለተቋሙ ደንበኞች ቀልጣፋ የባንክ አገልግሎት እንደሚሰጥ በተለይም የኢንተርኔት፣የሞባይል እና የክፍያ ካርድ የመሳሰሉትን የዲጂታል ባንክ አገልግሎቶች እንደሚያቀርብ አቶ ኪዳኔ ተናግረዋል፡፡ በተያያዘም ወጋገን ባንክ ከከፍታ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ ተመስርቶ የተፈራረመው ስምምነት የባንኩን ተደራሽነት በማስፋት ተጨማሪ ደንበኞች ለማፍራት እንደሚያግዘው አቶ ኪዳኔ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
የከፍታ ማይክሮ ፋይናንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሞገስ ታመነ በበኩላቸው ከወጋገን ባንክ ጋር የገቡት ስምምነት ለደንበኞቻቸው የላቀ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችላቸው ተናግረው ስምምነቱ የተሳካ ውጤት እንደሚያስገኝ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡
ከፍታ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ/ማ የሰራተኞች የስድስት ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና ግምገማ ተካሄደ።
በሁሉም ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት የሚገኙ የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች የስድስት ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርታቸዉን ጥር 8 እና 9 አዲስ አበባ ለዋና መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራር እና ለቦርድ አመራሮች አቅርበዋል።
በሪፖርቱ መሰረት የቦርድ አመራሮቹ የተጀመረዉ ስራ ጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለ እና ለወደፊቱም ከዚህ በበለጠ ለጥሩ ዉጤት ጠንክረዉ መሰራት እንዳላባችዉ እና አስፈላጊ በሆኑ ነገሮቸ ሁሉ ቦርዱ ከጎናቸዉ እነደሚሆን ገልጸዋል።




ከፍታ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ/ማ
ውድ ደንበኞቻችን አጋር ድርጅቶችና የከፍታ ማ/ፋ/ተቋም ባለአክሲዩኖች እንኳን ደስ
አላችሁ፡፡
ከፍታ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ቀደም ሲል ከብሔራዊ ባንክ ባገኘው ፈቃድና ከፌዴራል የንግድ
ሚኒስቴር የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ተመዝግቦ በሁለት ቅ/ጽ/ቤቶች በአዲስ አበባ ከተማ ስራ
መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣ ብሎ በአዳማ፣ በሆሳዕና ፣በአዋሳ እና በወልቂጤ አራት
ቅርንጫፍ በመክፈት የስራ እንቅስቃሴውን አስፍቷል፡፡
በ89.4 ሚሊዬን የተፈረመና በ57.6 ሚሊዬን በተከፈለ ካፒታል የስራ አድማሱን በማስፋት
ስራውን በ ዚህ ቅ/ጽ/ቤቶች ጀምሯል ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የተቋሙ ሀብት ወደ 57.4 ሚሊዬን የደረሰ
ሲሆን ከፍታ ማ/ፋ/ተ/አ/ማ ለየት ባለ የስራ እንቅስቃሴው የራሱን ኮርባንኪንግና የዳታ ሴንተር
በመገንባት ወደ ሥራ የገባ ከአንጋፋዎቹ ማ/ፋ/ተቋማት ተርታ የሚመደብ ተቋም ሁኗል፡፡
በተቀናጀ የቦርድ አባላት እገዛና የስራ አመራሩ ጥረት እንዲሁም በቅ/ጽ/ቤት በሚገኙ የስራ
ክፍሎቹ በአዲሱ የበጀት አመት 2400 የብድር ደንበኞች 1200 የቁጠባ ደንበኞቹን መሰረት አድርጎ
164.2 ሚሊዬን ብር ለማሰራጨት እና 145.5 ሚሊዬን ብር ተሰብሳቢ ገንዘብ ለማድረስ አቅዷል፡
፡
ተቋማችን በደንበኞቻችን ፍላጎት መሠረት ባደረገ የፍላጎት ቁጠባ የብድር አቅርቦት ደንበኞቸ
እንዳሉበት መልከአምድር የሥራ ምህዳሩን እያሰፋ ይገኛል፡፡ የቡድን ብድሮች፣የግል ብድሮች፣
የፍጆታ ብድር ለንግድ ማስፋፊያ እና የአጫጭር ጊዜ ብድሮችን ከአስቤዛ የብድር አይነት ጋር
ይዞ ለደንበኞቹ ቀርቧል፡፡
በጅምር ሂደታችን እ.ኤ.አ. በሰኔ 2024 በተቀላጠፈ ሁኔታ በሁለት ቅ/ጽ/ቤት የጀመረው ዛሬ ላይ
በስድስት ቅ/ጽ/ቤቱ የስራ አድማሱን አስፍቷል፡፡
አሁን ያለንን የኮርባንኪንግ ሲስተም በመጠቀም ወደሞባይልና ዲጅታል ባንኪንግ ለመግባት
ከክራፍት ሲልከን ሊሚትድ የሶፍት ዌር አቅራቢ ድርጅት ጋር የስራ ስምምነት በማድረግ ወደ
ትግበራ ገብቷል፡፡
ከደንበኞቻቸን ጋር ለመስራት የደንበኞችን እርካታ መሰረት ባደረገ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት ወደ
ስራ ገብተናል፡፡
መጪው የስራ ዘመን የልማት፣የእድገት፣የከፍታ ዘመን እንዲሆንልን እየተመኘን የከፍታ
ማ/ፋ/ተቋም የቦርድ አባላት የሥራ አመራርና የቅ/ጽ/ቤት ሠራተኞቻችን በትጋት ለመስራት
ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል፡፡
Greatness together
በአብሮነት ወደ ከፍታ እንጓዝ
Some Branch Photo
News: Kefeta Microfinance Institution S.C Inauguration ceremony







News: Kefeta Microfinance Institution S.C Inauguration ceremony


